Tour and Travel

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ መኪኖች ማለትም 2 ዳም ትራክ መኪና፣ 2 ሲንግል ካፕ መኪና፣ 1 ደብል ካኘ መኪና እና 2 40 ሰው የሚይዝ አውቶቡስ ለ2 ወራት የኪራይ አገልግሎት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር: ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/05/2019

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ መኪኖች ማለትም 2 ዳም ትራክ መኪና፣ 2 ሲንግል ካፕ መኪና፣ 1 ደብል ካኘ መኪና እና 2 40 ሰው የሚይዝ አውቶቡስ ለ2 ወራት የኪራይ አገልግሎት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::

2. ጨረታው ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ህዳር 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ.ቁጥር 1000057735167 በመክፈልና የባንክ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡

አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘጓሕ ሆስፒታል አካባቢ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ፣

ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008

ስልክ ቁጥር 0115 586 725

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡

7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መጃ በስልክ ቁጥር 0115 58-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-13 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tana Beles Sugar Factory
  • Bid bond: 1% በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 02, 2026)
  • Posted at: 2026-11-03T11:38:19.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders