Construction Machinery

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የተለያዩ ማሽነሪዎችን በኪራይ ለማሠራት በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ መንገድ ልማት ሥራዎችን ለማከናወንና የተለያዩ ማሽነሪዎችን በኪራይ ለማሠራት በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ~

ሀ) የማሽነሪና ዓይነት -

  • ግሬደር የፈረስ ጉልበት 217 HP ከዚያ በላይ ብዛት 2
  • ሎደር የፈረስ ጉልበት 217 HP ከዚያ በላይ ብዛት 3
  • ኤክስካቫተር የፈረስ ጉልበት 240 HP ከዚያ በላይ ብዛት 1

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡

  1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
  6. የተመሰረቱበት ዓመት እ/ኤ/አ ማሽነሪዎች 2014 ከዚያ በላይ
  7. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  9. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስ/ ፋይናንስና/ኢኮ/ል/ መምሪያ

ሀዋሳ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-16
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-16 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 250,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
  • Posted at: 2026-11-06T07:22:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders