Food Items and Drinks
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት ጽሕፈት ቤት ታኅሣሥ 01/2019 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ ለ7 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለሕግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ፣ ጥሬ እህል፣ ማጣፈጫ ሸቀጣሸቀጦች እንዲሁም የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ም/ሸዋ ዞን መ/ቤት መምሪያ ታኅሣሥ 01 /2019 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ ለ7 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለሕግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማኅበራትም ሆነ ግለሰብ እንዲሁም ጥሬ እህል የማጣፈጫ ሸቀጣሸቀጦች እንዲሁም የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችና ነጋዴዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው፡፡
- በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስከር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት TOT እና TIN ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረ ቼክ (CPO) እና የእህሉን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለማሰናከል የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጪ ሆኖ ወደ ፊት ለሚደረገው ማንኛውም ጨረታ ላይ የማይሳተፍ መሆኑንና ያስያዘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾቹ በከተማ ውስጥ የእህል ማከማቻ መጋዘን ያላቸው ወይም ማዘጋጀት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማ/ቤት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ላይ ተጫረቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ኮሚቴዎች እና የማ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት ከነ ገንዘብ ጽ/ቤት እና ከዞኑ አቃቤ ሕግ በሚወከሉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የእህሉን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ስም አድራሻ ሕጋዊ ማህተም ፈርማማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዞኑ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በግዥና ፋይናንስ አስተዳደደር መግዛት ይችላሉ ::
- በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ለተደራጁ ማህበራት የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት ቀን አንስቶ እስከ 3 ቀን በማ/ቤቱ በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ማ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ውል ሰጪ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኝው ውሉን የማሰረዘም ወይም የማቋረጥ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ወይንም የምግብ እህሉን በራሳችሁ ማጓጓዣ እስከ ማረሚያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ባሸነፈበት የዕቃ ዝርዝር ውል ተፈራርመው በ5ት ቀን ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡት ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- በጨረታው ውል መሰረት እህሎችን ሙሉ ለሙሉ ካስገቡ በኋላ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል ፡፡
- ማ/ቤቱ የጠየቀውን ያህል ባንዴ ተጠቃሎ መግባት አለበት፡፡
- ውል ተቀባዩ በማናቸውም ምክንያት በዋጋ ማቅረቢያው ከቀረበው ዋጋ ውጪ የዋጋ ለውጥ ሊያደርግ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሃደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ ::
- ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማቤቱ ለበላይ አካሎች ቅሬታ ጨረታው ከተከፈተበት አንስቶ እስከ 5ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ የደ/ም/ሸ/ዞን ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0113411190/ 0113410023/
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-24 10:30
- Bid opening (note): ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: South West Shewa Zone Prison Department
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T07:59:43.000Z
- Source: Qelal Tenders