Food and Beverage
የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የቀለብ ጤፍና በቆሎ፣ የምግብ ዘይት፣ ምስር፣ አተር ክክና ጓያ ክክ እና የእንሰሳት መድሃኒት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የገዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት አመት ለአስተዳደር ጽ/ቤት በሎጀስቲከስ አገልገሎት የሚውል
- ሎት1 የቀለብ ጤፍና በቆሎ፣
- ሎት፡ 2 የምግብ ዘይት
- ሎት፡3 ምስር፣አተር ከከ እና ጓያ ክክ
- ሎት፡4 የእንሰሳት መድሃኒት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉና ለሎት2 የቫት ሰርተፍኬት ማስያዝ ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ/ክሊራንስ) ማያያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1፡ 24,000/ሃያ አራት ሺህ ብር ለሎት2፡- 3000 ብር /ሶስት ሺህ ብር/ ሎት3፡- 6000 /ስድስት ሺህ ብር/ ሎት4፡- 15000 /አስራ አምስት ሺህ / በመሂ1 ወይም በ C.PO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር-3 በመምጣት የማይመለስ 200 ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- ውድድሩ በሎት ወይም በድምር ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት እና በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም ስምና ፊርማ ማድረገ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ሰነዱ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለው ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
- ይህ ግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ10 ቀን በአየር ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 በግልጽ ይከፈታል፡፡ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምር ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡በተገለጸው የጊዜ ገደብ ያልቀረበና ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል።
- አሸናፊው ሎት 1 ሎት፡-2 ፡ሎት፡3 እና ሎት፡4 ጽ/ቤቱ ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የመንግስትን የግዥ መመሪያ አዋጅና ከላይ የተዘረዘሩትን ማዘዣዎች ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582460316/0141 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን
ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-16
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-16 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Baso Liben Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T08:30:54.000Z
- Source: Qelal Tenders