Software Provision, Development and Web Design

ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የሂሳብ አሰራሩን በቴክኖሎጂ ለማገዝ እና ዲጂታላይዝ ለማድረግ (ሶፍትዌር በማበልጸግ እና የተለያዩ የቁጠባ፣ ብድር፣ የሰው ኃይል እና ቅርንጫፍ አገልግሎቶችን በማካተት ስልጠና ጭምር ለመስጠት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ካፋ  የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የሚገኘው ዩኒዬን በዞን ውስጥ ከሚገኙ ዩኒዬኖች አንዱ ሲሆን በ2019 በጀት ዓመት የሂሳብ አሰራር በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆንና ድጂታላይዝ ለማድረግ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ዩኒዬኑ ባለው ሰርቨር ላይ ሶፍት ዌር ማስበልጸግ ይፈልጋል።

ስለሆነም ሶፍት ዌሩን በማበልጸግና የተለያዩ የቁጠባ አይነቶች የብድር አይነቶች፣ አነስተኛ የብድር ኢንሹራንስ አገልግሎት፣ የሰው ኃይል አስተዳደርና ቅርንጫፍ አገልግሎት ያካተቱ መረጃዎችን በማስገባት በዘርፉ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና በመስጠት አገልግሎት ማስጀመር የሚችል ማንኛውም ህጋዊ አቅራቢ መወዳደር ይችላል።

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  3. ቫት ተመዝጋቢ የሆነና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፤
  5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ወይም /supplier list/ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ስለመሆኑ ማቅረብ የሚችል፤
  6. ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ የሆነ፤
  7. ባለፉት 4 ተከታታይ ዓመታት በአንዱ ማለትም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በአንዱ በተመሳሳይ ተቋማት ማለትም ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ዩኒዬኖች ወይም የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት መስራቱን የሚያረጋግጥ መልካም የሥራ አፈጻጸም መቅረብ የሚችል፤
  8. በኢንሳ /Ethiopia cyber security/ የተረጋገጠና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  9. ማንኛውም CPO ብር 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችልና መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች የማይመለስ ብር 500 በአካውንት ቁጥር 1000029085262 ገቢ በማድረግ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ 03 ቀበሌ ቦንጋ መምህራን ት/ት ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው በዩኒዬኑ ጽ/ቤት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  10. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ዶክመንት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግና በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
  11. ጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ሰዓት የሚሸጋገር ይሆናል።
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለበለጠ መረጃ፡- 047 331 0583/ 09 17 86 63 60/ 09 12 13 23 82/ 09 02 50 83 26 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ካፋ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተወሰነ ኅብረት ሥራ ዩኒየን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Kafa Save and Credit Cooperative Union PLC
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T08:51:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders