House and Building Sale

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 84/2016 በአንቀጽ 55 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጋራ ህንጻዎች ስር የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በጨረታ እንደሚሸጥ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በካፒታል ፕሮጀክት ተገንብተው በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ንግድ ቤቶችን በ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ በግልጽ ጨረታ ያቀረባቸውን ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከ25/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ከዚህ በታች በተገለፁት ቦታዎች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ተ.ቁ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ሥፍራዎች

የሚገኝበት አድራሻ

1

አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት

ባምቢስ ግሪክ ትምህርት ቤት አካባቢ

2

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰሜን ቅርንጫፍ

ለሚኩራ ክ/ከተማ ቦሌ አራብሳ ሰፈራ አደባባይ አካባቢ

3

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ደቡብ ቅርንጫፍ

ንፋስ ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፉሪ ሃና ሳይት

4

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ

ለሚ ኩራ ክ/ከ ቦሌ አያት 49 ሳይት

5

ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምዕራብ ቅርንጫፍ

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወርቁ ሰፈር

በተጨማሪም በኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች

  • ፌስ ቡክ (Face book): https://www.facebook.com/aahdpo.gov.et 
  • ቴሌግራም (Telegram): https://www.com/aahdc_official መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-11-27
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ ከ25/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11፡30
  • Bid opening: 2026-11-27 17:30
  • Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Housing Development Corporation
  • Buyer's registered address: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 1 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው አዲስ ሕንፃ
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
  • Posted at: 2026-11-07T09:20:33.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders