Office Machines and Accessories

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉስሴ ክስ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት (Addis Ababa City Administration Revenue Bureau-Guellele Sub City Small Tax Payers Branch Office) – 001/2019

ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ለ2019 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ፡-

  • ሎት 1፡- የጽህፈት መሣሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 2፡- የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3፡- ህትመት
  • ሎት 4፡- የደንብ ልብስ
  • ሎት 5፡- የተሽከርካሪ ጎማ፣ ባትሪ እና የመኪና ጌጣጌጥ
  • ሎት 6፡- የቢሮ ወለል ምንጣፍ እና መጋረጃ
  • ሎት 7፡- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
  • ሎት 8፡- ኮምፒውተርና ተዛማጅ የአይቲ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 9፡- የህንጻ መሣሪያዎች ዕቃዎች
  • ሎት 10፡- የቢሮ ፈርኒቸር
  • ሎት 11፡- ለሰራተኛ ክበብ የሚሆኑ መገልገያ ዕቃዎች እና የውሃ ሳኒተሪ /ሲንክ የዕቃ ማጠቢያ ዝርጋታ ስራ
  • ሎት 12፡- ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 13፡- ልዩ ልዩ የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና
  • ሎት 14፡- የጀነሬተር ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 15፡- የጀነሬተር ጥገና
  • ሎት 16፡- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፋክስ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ስካነር እና ኤሌክትሮኒክ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ መለዋወጫ ዕቃዎች
  • ሎት 17፡- የተለያዩ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ጨምሮ፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፋክስ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ ስካነር እና ኤሌክትሮኒክ ጥገና
  • ሎት 18፡- ቆሎ
  • ሎት 19፦ የታሸገ ውሃ

በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ብቁ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርቡ ወይም (online የተመዘገቡ)።
  3. የ6 ወራት ያላለፈው የጨረታ መወዳደሪያ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በመ/ቤቱ የጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል። ካልተጠቀሰ ዋጋው ተ.እ.ታን(VAT) እንዳካተተ ተደርጉ ይወሰዳል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት።
  7. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ አጠገብ ቃሲም ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክ/ከተማ አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000378561829 (4054) ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በማምጣት ከግዥ አገልግሎት ቡድን ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ፋይናንሻል እና የቴክኒክ ሰነድ ዋናውን ዶክመንት፣ ፎቶ ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ 2% ለየብቻው በታሸገ እንዲሁም የድርጅቱ ስም፣ ስልክ ቁጥራቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም እና የሚረቱበትን የጨረታ ዓይነት ምድብ በመጻፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ጊዜው የሚያበቃው በ11/3/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት እንቁላል ፋብሪካ ፖሊስ መኮንኖች ክበብ አጠገብ ቃሲም ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ በግዥ አገልግሎት ቡድን ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  9. ጨረታው በዚያኑ ዕለት ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ ልክ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ የግዥ አገልግሎት ቡድን ውስጥ ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 12፣ 13፣ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም ሎት 3-ህትመት ላይ የኮንትራት ስምምነት ለሚጠየቀው ብቻ ለእያንዳንዱ ምድብ ብር 6000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ምድብ/ሎት/ ግን የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉስሴ ክፍስ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤ ጨረታውን ለማዛበት የሚሞከር ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  12. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  13. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ዕቃ ዋጋው 10% ማስያዝ መዋዋል ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪሎት12፣ 13፣ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም ሎት 3 ህትመት ላይ የኮንትራት ስምምነት ለሚጠየቀው ብቻ ለእያንዳንዱ ምድብ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  14. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ዕቃዎቹን መ/ቤቱ ስቶር ድረስ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በማጓጓዝ ያቀርባል።
  15. ለዓመታዊ የኮንትራት ዕቃዎችና አገልግሎት አሸነፊ ድርጅት ከመ/ቤቱ ውል ከገባበት ጀምሮ ለተከታታይ 6 ወራት የተጠየቀው አገልግሎት ሆነ ዕቃዎች በቀረበው ዝርዝር ስፔስፌኬሽን መሰረት እያቀረበ ያለ ከሆነ በወቅቱ የገበያ ጥናት ተደርጉ የዋጋ ማስተካከያ ሊያደርግ ይችላል።
  16. አነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ አካላት ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይገባቸዋል። የደብዳቤው ይዘትም ተጫራቹ በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት በኋላ አቋርጦ ቢወጣ ለሚፈጠረው ክፍተት ዋስትና የሚሰጥ መሆን ይገባቸዋል።
  17. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በተገለጸው የመጫረቻ የሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ ተቀባይነት የለውም፤ በተጨማሪም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈጸሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  18. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ሆነ የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚፅፉት ማንኛውም አስተያየት ተጨባጭ እና ሊረጋገጥ የሚችል መሆን ይኖርበታል፤ ግልፀኝነት በሚጎድልበት ጉዳይ ላይ ተጫራቾች መከራከር አይችሉም።
  19. በጨረታ መወዳደርያ የሚቀርቡ ዋጋ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል። ሆኖም ግን የኮንትራት ስምምነት ዕቃ ግዥ ሆነ አገልግሎት አይመለከተም።
  20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃ ብዛት 20% ቀንሶ ወይንም ጨምሮ ከአሸናፊ ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  21. ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር/ 011-126-5006 ወይም 011-156-7198 በጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የግዥ አገልግሎት ቡድን በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
  • ማሳሰቢያ፡- ቅዳሜ እስከ 10:30 ሰዓት ስስራ ክፍት ሆኖ ይውላል፤ እንደ ስራ ቀንም ይቆጠራል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Revenue Bureau Gullele Sub City Small Tax Payers Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-09T12:11:43.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders