Textile, Garment and Leather
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታመቂያ
የጨረታው ቁጥር 03/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 - የሰራተኛ የደንብ ልብስ
- ሎት 2፡- ህትመት
- ሎት 3 - ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 4 ፡- የማሽን ጥገና
- ሎት 5 ፡- የግቢ አጥር ጥገና
በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች፡-
1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የአጥር ጥገና ላይ ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በደረጃ አምስት(5) እና በላይ መሆን አለባቸው። ቅድመ ክፍያ የሚሰጠው ስራው ከ50% በላይ ሲሆን ብቻ ይሆናል።
3. የእቃዎች ዋጋ 15% ቫት ተጨምሮ ይቅረብ። ባይቀርብ እንደ ተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል ከአጥር ጥገና ውጭ በጥቃቅን እና አነስተኛ በአምራችነት ተደራጅተው የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።
4. ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት የሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ማሰገባት አለባቸው።
6. ተጫራቾች ለሎት1-8,000 - ለሎት2፡-2,000 - ለሎት3፡-2,000 - ለሎት4፡-3,000 - ለሎት5፡- 30,000 ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የተመረጡ እቃዎች እና ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን በቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይችላሉ።
9. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
10. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጭ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማምጣት አለባቸው። ት/ቤቱ ተጨማሪ በእቃዎች ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
11. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 01 የሚከፈት ይሆናል።
12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር-011 154 2095
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-20 09:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulelle Sub City Education and Training Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-09T12:48:22.000Z
- Source: Qelal Tenders