Building Construction
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ. አሁን በኪራይ እየተገለገለበት የሚገኘውን ቦሌ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘውን ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ የእድሳት ስራ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር: ፀኢ/ግንአመ/09/2026
የቀለም ቅብ፣የበር መዝጊያ ቁልፎች ፣ የቧንቧ መክፈቻና መዝጊያ እድሳት ጨረታ ማስታወቂያ ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ አዲስ ወደገነባው የራሱ ዋና መ/ቤት ህንጻ ለመዛወር በዝግጅት ላይ ይገኛል፤ በመሆኑም አሁን በኪራይ እየተገለገለበት የሚገኘውን ቦሌ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘውን ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ የእድሳት ስራ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ያላቸው ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡
1. የሚከናወኑ ስራዎች
- የቀለም ቅብ ዕድሳት ስራ
- የኤሌክትሪክ መስመር መስተካከልና መብራት መቀየር ስራ
- የበር ቁልፎች መተካከል ስራ
- የውሃ ቧንቧ መክፈቻና መዝጊያ የጥገና ስራ
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Security)
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 30,000.00 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማስከበሪያው በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በታወቀ የሀገር ውስጥ ባንክ የተሰጠ ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) መሆን አለበት። የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ20 ቀናት ጸንቶ መቆየት አለበት፡፡
3. ተጫራቾች የሥራውን ሁኔታ ፡- የቦታ ምልከታ (Site Visit) እና ዋጋ ማቅረቢያ ጊዜ፡
- ከህዳር 2 ቀን 2019 እስከ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል በቦታው በመገኘት ህንጻውን መጎብኘት ይችላሉ፤
4. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ፡
- ጨረታው ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ማሳሰቢያ፡ ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡ ጸሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት (የግዥ ክፍል)፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 106
- ከመገናኛ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ ቀለበት መንገድ፣ ከቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ: 011-111-97 70/71 ወይም 011-111-98 27
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-11-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-14 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsehay Insurance S.C.
- Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T07:34:04.000Z
- Source: Qelal Tenders