Building Construction
የብራና ማተሚያ ድርጅት በሚያቀርበው የግንባታ ዲዛይን እና የቴክኒክ መስፈርት መሠረት የህንፃ ግንባታ ስራዎችን ህጋዊ በሆኑ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር ፡BM/NCB/
CW/03/2019
የብራና ማተሚያ ድርጅት በሚያቀርበው የግንባታ ዲዛይን እና የቴክኒክ መስፈርት መሠረት የህንፃ ግንባታ ስራዎችን ህጋዊ በሆኑ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. ደረጃቸው GC/BC 1 እና 2 የሆኑ፣
2. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የ 2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (T) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በብራና ማተሚያ ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት፣ ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ፋይናንሽያል ዶክመንት እና ቴክኒካል ዶክመንት አርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። (ቀኑ የሳምንቱ እረፍት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል)።
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡
አድራሻ፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት፣ አዲስ አበባ የቢሮ ቁጥር፡ 26
ስልክ ቁጥር፡ +251-11-4421664
ዌብሳይት / ኢሜይል፡ [email protected]
የብራና ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-24 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት አስራ አምስተኛው (15ኛው) ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Branna Printing Enterprise
- Buyer's registered address: ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T08:01:32.000Z
- Source: Qelal Tenders