Water Pipes and Fittings

የግንደወይን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግንደወይን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

በመሆኑም፡-

  1. በመስኩ የተሰማሩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽሀ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት (ቫት) ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ድረስ በፖስታ አሸጎ በማስገባት ነው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በመ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ከጨረታ ፖስታው ጋር አብሮ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 4 ለገቢ/ግዥ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ለጨረታ ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ዋጋ ማቅረቢያና ፖስታቸው ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውንና ስማቸውን መፃፍ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይውላል፡፡
  7. የጨረታ መዝጊያ ቀኑ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
  8. ጨረታው የሚከፈተው በ16 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በመክፈቻ ቀኑ ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸውን ካላኩና ካልመጡ ጨረታው በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፈው የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ባቀረበ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
  11.  አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለጸለት ቀርቦ ዉል ከያዘ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያዉ አንድ በመቶ ብር የሚመለስ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የሚያሲዝ መሆኑን እና ያስያዙት ብር የሚመለሰው በወጣው መስፈርት መሰረት እቃው በባለሙያ ተረጋግጦ ተቀባይነት ካገኘና አርክክብ ከጽ/ቤቱ ጋር ከተደረገ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን በጨረታው መሰረት እቃውን ካላቀረበ 10 በመቶ ውርስ ይሆናል፡፡
  13. እቃዉ በእቃ ጥራት ባለሙያ እየተረጋገጠ ከ/ቤቱ ንብረት ክፍል ጋር እርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊዉ ተጫራች ያሸነፈዉን እቃ ግ/ወይን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡
  15.  ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጽ/ቤቱ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት 25 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
  17. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  18. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  19.  የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም 
  • በስልክ ቁጥር 058 664 00 73 መደወል ይችላሉ፡፡
  • ማሳሰቢያ፦ የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽሀ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የግንደወይን ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-24
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-24 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Gendwoin ketema water service office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T12:32:28.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders