Water Pipes and Fittings
በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንጽህና መጠቀሚያዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት የቧንቧ መገጣጠሚያዎች፣ የንጽህና መጠቀሚያዎችን እና የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲገዙ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ድምር ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- የንጽህና መጠበቂያና የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊ የሚለየዉ በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
- የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች አሸናፊ የሚለየዉ በተናጠል ዋጋ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከጨረታዉ ዉድድር ማግለል የማይችል ሲሆን በጨረታ ሰነዱ የሰጠዉን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደበጀቱ ሁኔታ በጨረታዉ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸዉ የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዎቹን ሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን አስረክቦ ገንዘቡን ወጪ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 10 65 /033 222 04 83 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሐይቅ ከተማ መጠጥ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-11-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-24 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Hayk City Water and Sewerage Service Bureau
- Bid bond: 1%
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Be'kur (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T13:00:14.000Z
- Source: Qelal Tenders