Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase

የስልጤ ልማት ማህበር ሞተር ሳይክል እና የምጥን መኖ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የስልጤ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ሞተር ሳይክል እና ለሀይረንዚልዩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለበኬ የከብቶች እርባታ ማዕከል የወተት ላም ፣የጥጃ እና የድለባ በፊ የምጥን መኖ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤

ስለሆነም

1. ለ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግል የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤

2. የጨረታ ማስከበሪያ ለሞተር ሳይክል የ25,000 ብር እንዲሁም ለምጥን መኖው 20,000 ብር ቼክ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስይዝ የሚችል።

3. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ለሁለቱም የጨረታ አይነት ብር200.00/ሁለት መቶ/ በመክፈል ስልማ አ/አ ቅ/ጽ/ቤት ከረሜላ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 እና ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ስልማ ዋና ጽ/ቤት በመቅረብ በአካል መግዛት ይችላሉ።

4. ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 8፡30 ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል፡፡ 16ኛው የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን 01 ኦርጂናል እና 1 ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ በመብቱ የተጠበቀ ነው::

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 278 2974 /011 277 2176/046 771 12 93 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ::

የስልጤ ልማት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 8፡30
  • Bid opening: 2026-11-26 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 9፡00
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Silte Development Association
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T08:09:59.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders