Equipment and Accessories
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ሰሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ሰሴክተር መ/ቤቶች
- በሎት-01 የጽህፈት መሳሪያ
- በሎት-02 ኤሌክትሮኒክስ
- በሎት-03 ሞተር ሳይክል
- በሎት-04 ፈርኒቸር
- በሎት-05 ደንብ ልብስ- በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድና የስራ ፍቃድ፣
2. የቫት/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
3. ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፣
4. አግባብነት ያለውን የአቀራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ግዢ ክፍል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መወዳደር ይቻላል::
5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመመዳደሪያ ሰነድ ሳይ የድርጅቱን ማህተም፣ ስማቸውን፣ፌርማቸውን እና አድራሻቸውን በግልጽ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ዕቃ ዋጋ መሙላት የሚችሉት በመ/ቤታችን በተዘጋጀው በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉንና ሁለት የኦርጅናሉ ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ CPO በኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታ ውስጥ በማድረግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ያስያዙት CPO ለወደቁት ሲመሰለ ለአሸናፊዎች ግን ዕቃውን አቅርበው ሲጨርሱ ይመለሳል ::
10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ የዋጋ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም::
11. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የዕቃውን ናሙና አቅርቦ ተፈትሾና ተረጋግጦ በናሙናው መሰረት ዕቃው ኦርጅናል ብቻ ሲሆን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡
12. የጨረታ ስራን ሆን ብሎ ከጨረታ ማሸጊያ ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የጨረታ ስነ-ስርዓት ማወክና መረበሽ ከውድድር ውጪ ያደርጋል ፤በህግም ያስቀጣል፡፡
13. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይ//ጽ /ቤት ግዥ ክፍል ይከፈታል፤ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡
14. ጨረታውን ካሸነፋ በኋለ ዕቃውን ለማያቀርበው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO አይመለስም::
15. የዕቃው የመጨረሻ ርክክብ የሚፈጸመው ጨረታው በተካሄደበት በደቡብ/ም/ሲ/ህ/ክ/መንግስት በዋቻ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ጊቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
16. የዕቃው ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ለሰበት፡፡
17. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግዎ በሥ. ቁ 0473 38 04 51/ 59 መደወል ይችላሉ።
18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሣጥን መክፈቻ ስነ ሥርዓትን አያስተጓጉልም::
በደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መን በካፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-11-26 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሠዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Wacha City Administration FEDB
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
- Posted at: 2026-11-11T10:22:40.000Z
- Source: Qelal Tenders