Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ፡ደወ/ከፍ/425 /2019

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የተዘረዘሩትን እቃዎችና እንዲሁም የፎቶ ኮፒ አገልግሎት የፍትሐብሄር፣ ወንጀል፣ኮፒ እየተደረጉ ለሚመለከተው አካል የሚተላለፍ መዛግብቶችን ኮፒ ማድረግና ለዚህ አገልግሎት የቤት ኪራይ የመብራት ወጪዎችን በመ/ቤቱ ይሸፍናል፡፡ 

በዚህ መሰረት መ/ቤቱ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ሎቶች ለማጫረት ይፈልጋል፡- ማለትም

ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎችን ፣ ሎት 2 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን፤ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን፤ ሎት 4 የህትመት ስራዎችን፤ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ ሎት 6 የመኪና እቃ መለዋወጫ፣ ሎት 7 የደንብ ልብስና ተዛማጅ እቃዎችን፣ሎት 8 የፎቶ ኮፒ አገልግሎት/አወት ሶርስ/፤ ሎት 9 የመኪና ዘይቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን መ/ቤቱ ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው ፣

4. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ

5. የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔሲፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፣

8. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው ፣

9.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ደ/ወ/ዞ/ከፍ/ፍ/ቤት ግዥና ፋይ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 121 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያዎችን 12000/አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 2 ቋሚ አላቂ ዕቃዎችን 4000 /አራት ሺህ ብር ብቻ/፤ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን 3600/ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ብር ብቻ/፤ ሎት 4 የህትመት ስራዎች 7000/ሰባት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 10000/አስር ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 6 የመኪና እቃ መለዋወጫ 30000/ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 7 የደንብ ልብስና ተዛማጅ እቃዎችን/ 6000/ ስድስት ሺህ ብር ብቻ/ ፣ሎት 8 የፎቶ ኮፒ አገልግሎት/አወት ሶርስ/ 8000 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ ሎት 9 የመኪና ዘይቶች 4000 /አራት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት “ማስያዝ አለባቸው፡፡

11. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣

12. አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም ፡፡ ሆኖም በሎቱ ውስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንድ ዕቃ ዋጋ ሳይሰጥበት ቢቀር ተጫራቹ ድርጅት ከጨረታ ውጪ የሚሆን ይሆናል፡፡

13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን / ሰነዱን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ወ/ዞ/ከ/ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 412 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡

15. መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው፡፡

16. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋሉ፡፡

17. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠቅላላ ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

18. ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ፡፡

19. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033-111-44-28 ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-82-21 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-21 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: South Wollo Administration Zone High Court
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T10:08:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders