Textile, Garment and Leather

የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር- 0001/2019

የአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም፦

  • ሎት-1- የደንብ ልብሶች
  • ሎት-2- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት-3- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  • ሎት-4- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 5 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች
  • ሎት 6- ቋሚ እቃዎችን
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ የላብራቶሪ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ ሲፒኦ (CPO) ለእያንደንዱ ለሚሳተፍበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡

6. ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው፡፡

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት /በሂሳብ ቁጥር 1000014692731 ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በማስገባት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 በፋይናንስ በማወራረድ በትምህርት ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሽገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11:30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

9. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

1

ሎት 1- የደንብ ልብስ

42,000

2

ሎት -2 አላቂ የቢሮ እቃዎች

20,000

3

ሎት -3- አላቂ የትምህርት እቃዎች

16,000

4

ሎት -4- አላቂ የፅዳት እቃዎች

20,000

5

ሎት -5- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

8,000

6

 ሎት -6- ቋሚ እቃዎች

20,000

7

ሎ-ት-7- ልዩ ልዩ የላብራቶሪ እቃዎች

6,000

10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታውን አሽናፊ ሆነው ከተገኙ በኃላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡

12. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡

13. በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማፃፍ፡ እና ለማያመርቱት ምርት /ዕቃ/ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

14. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በትምህርት ቤቱ በፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 22 ይከፈታል፡፡

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-4-71-61-31 / 011-4-34-30-96

አድራሻ፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከወረዳ ሁለት ፊት ለፊት በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

አቃቂ ብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Bruh Tsefa Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T10:04:08.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders