Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለኮሌጁ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለኮሌጁ የሚያገለግሉ ለስልጠና ዕቃዎች፤ ለቢሮ ዕቃዎች ለፅዳት ዕቃዎች የቋሚ ዕቃዎችና ለደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ።

ሀ/ የተወዳዳሪዎች መመሪያ

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፊቃድ እና የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚገልጽ መሆኑንና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ በቂ ማስረጃ ከመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

2. ማንኛውም ተጫራች ከ100,000 (አንድ መቶ ሺህ) የግዥ ግምት በላይ የሚጫረት ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢ መሆን አለበት።

3. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስናና የብክነት ድርጊቶች ነጻ የሆነና በፌዴራልና በክልል የወጡትን የግዥ መመሪያ እና ደንቦችን የሚያከብሩ ስለመሆኑ ሰነዱ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምኖበት መፈጸም ይኖርባቸዋል።

4. ከጨረታ ሰነድ ጋር የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ፧

5. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት የጨረታ ሰነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ በስራ ሠዓት በኮሌጁ ጽ/ቤት በመገኘት ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይቻላል።

6. ጨረታውም በወጣ በ15ኛው ቀን ልክ በ11፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ስሆን ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ) ብር በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።

7. አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ኮሌጁ ድረስ በራሱ ወጪ ማድረስ የሚችል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለዝርዝር መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 09 13 64 95 78 / 011 187 0598 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የጎሐጽዮን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት
  • Bid opening: 2026-11-25 17:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ልክ በ11፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Goha Tsion Technical and Vocational Training College
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T10:14:13.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders