Textile, Garments and Uniforms

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2019 በ 09/03/2019

  • የተለያዩ አልባሳት፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ጫማዎች፣
  • የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣
  • የሞባይል ግላሶች እና ከቨሮች፣ 
  • የእጅ ሰዓቶች ፣
  • ስፔርፓርቶች
  • የእይታ ዕቃዎች፣ መነፅሮች፣
  • መሬት ምንጣፍ፣
  • ኮስሞቲከስ እና  መዋቢያዎች፣
  • የኮንስትራክሽን እቃዎች፣
  • የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች
  • የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
  • የእስፖርት መስሪያ መሳሪያዎች፣
  • የተለያዩ አርቴፍሻል ጌጣጌጥ 
  • ምግብ ነክ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎቸ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. የታደሰ በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ አና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ሙድአነኖ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመከፈል ሰነድ ለመግዛት ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
  5. ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈል ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
  6. ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጭረት ለኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበረ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  7. በሀራጅ ጨረታ ለመጡት በእያንዳንዱ ኮዶች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  8. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በለሰቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ ከ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፈለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒአ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለባስልጣኑ መ/ቤት ግቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  12. የጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46)

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-18
  • Bid closing time: 08:00
  • Bid opening: 2026-11-18 10:00
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T08:59:41.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders