Equipment and Accessories

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ እቃዎች በሃራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሃራጅ ቁጥር 10/2019

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ሳይፈፀምባቸው የተወረሱ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፤
  • ኮስሞቲክስ፤
  • የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣
  • ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) አዳዲስ አልባሳት /የመጋረጃ ጨርቅ/ እና
  • የኮንሰትራክሽን እቃዎች በሃራጅ ጨረታ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤-

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
  2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ ሰነዱን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
  4. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ስዎች መሳተፍ አይችሉም።
  5.  በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤
    • ለምድብ 1 አዳዲስ አልባሳት የመጋረጃ ጨርቅ.......... 3,915,400.00 ብር
    • ለምድብ 2 ተሽከርካሪ መለዋወጫ.............................. 684,000.00 ብር
    • ለምድብ 3 ተሸከርካሪ መለዋወጫ............................. 102,700.00 ብር
    • ለምድብ 4 ተሸከርካሪ መለዋወጫ ..............................26,100.00 ብር
    • ለምድብ 5 ተሸከርካሪ መለዋወጫ.............................. 618,700.00 ብር
    • ለምድብ 6 ኮስሞቲክስ ..............................................406,400.00 ብር 
    • ለምድብ 7 ኤሌክትሮኒክስ ........................................119,100.00 ብር
    • ለምድብ 8 አዳዲስ አልባሳት.....................................37,300.00 ብር
    • ለምድብ 9 ኮስሞቲክስ ..............................................2500.00 ብር 
    • ለምድብ 10 ኤሌክትሮኒክስ ....................................... 110,000.00 ብር
    • ለምድብ 11ኮንስትራክሽን ማቴሪያል.............................213,500.00 ብር 
    • ለምድብ 12 ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ..........................250,600.00 ብር
    • ለምድብ 13 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) .........................33,300.00 ብር በ (Customs Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ _ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  6.  በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አከባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ አበባ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 4፡06 ሰዓት መጫረት ይቻላል።
  7. በሃራጅ ጨረታ እቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥይሆናል።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 / ሶስት የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
  10. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  11.  ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
  12.  ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆነን እናሳስባለን።

 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቀበት እንድሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፦

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

የጨረታዉ አይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

ስልክ ቁጥር

1

ኮስሞቲከስ

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

0221118429/

0222118925

2

ኤሌክትሮኒክስ

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

0221118429/

0222118925

3

አዳዲስ አልባሳት/የመጋረጃ ጨርቅ/

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

 

0221118429/

0222118925

4

የተሸከርካሪ መለዋወጫ

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

0221118429/

0222118925

5

ኮንስትራክሽን እቃዎች

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

0221118429/

0222118925

6

ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)

ሃራጅ

03/03/2019

08/03/2019

4:00

09/03/2019

0221118429/

0222118925

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙትን ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግና እቃው በድጋሜ ጨረታ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።ለተጨማሪ መረጃ፡-
  • አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): 08/03/2019፣ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-18 10:00
  • Bid opening (note): 09/03/2019
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T10:06:22.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders