Cleaning and Janitorial Equipment and Service
ስኬት ባንክ አ.ማ. የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationeryOffice Supplies and Services
Addis Ababa
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር SB/OT/NCB/12/04/2026
ስኬት ባንክ አ.ማ የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ፡- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ወቅታዊ የሆነ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸውን ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers List/ ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የስራ ሰዓት /ከሰኞ እስከ ቅዳሜ/ ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር /በመክፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የስራ ቀን በባንኩ ዋ/መቤት ቢሮ ቁጥር 407 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈተው የሳምፕል ውጤታቸው ብቁ የሆነ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች አንድ ቴከኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኮፒ ሰነድ እና አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ ለየብቻው በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ለዕቃዎቹ ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚመልሱበት ጊዜ በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው ልክ ናሙና /Sample/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ቅጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ያልታሸገ ሰነድ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያሰርዛል።
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ይመለስላቸዋል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፊርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው መከፈቻው ቀን በስራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመከፈቻው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በሚውልበት ቀን እና ሰዓት መሰረት ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመከፈቻ ስነ- ስርዓት ሰዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የዕቃ ዓይነት |
Cpo or unconditional bank guarantee |
|
1 |
የጽህፈት እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ |
250,000 |
- የባንኩ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2፡00 –11፡00 ብቻ ነው።
አድራሻ፡- ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡ 0111 275 585
ስኬት ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-11-30
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን በ5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-30 11:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን በ5፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Siket Bank S.C.
- Bid bond: 250,000.00 ብር
- Bid document price: 600.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 12, 2026)
- Posted at: 2026-11-12T08:43:39.000Z
- Source: Qelal Tenders