Textile, Garment and Leather
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በመደበኛ በጀት እና የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ በስፖርት ም/ቤት በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በመደበኛ በጀት እና የተለያዩ የስፖርት ትጥቅ በስፖርት ም/ቤት በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
- ሎት 2. ደንብ ልብስ የተዘጋጁ
- ሎት 3 ደንብ ልብስ ጫማ
- ሎት 4 የስፖርት ትጥቅ
- ሎት 5. የጽ/መሳሪያዎች
- ሎት 6. የጽዳት እቃዎች
- ሎት 7. የውሃ ማከሚያ ሪኤጀንት
- ሎት 8 የመኪና ጎማዎች
- ሎት 9. የመኪና እቃዎች
- ሎት 10. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 11. ቋሚ እቃዎች
- ሎት 12. የግንባታ እቃዎች
ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ በዘርፉ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች
1. በዘመኑ የታደሰ ተዛማጅ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (ማቅረብ የሚችሉ )
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው ( ማቅረብ የሚችሉ )
3. የታክስ ክሪላንስ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል
4 .የግዥ መጠን ከ500,000 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች የሞሉት ጨረታ ሰነድ ላይ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር ያልተሞላ ካለ ከጨረታው ውድቅ ይሆናል።
6. የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ/ ስፌስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ በብር መ/ቤታችን በወሰነው የጨረታ ዋስትና ማለትም ሎት1፡- 20,000 ብር ሎት2.፡- 20,000 ብር ሎት3፡ 20,000 ብር ሎት4፡- 20,000 ብር ሎት5. 60,000ብር ሎት6 ፡ 10,000 ብር ሎት7፡- 10,000 ብር ሎት8.፦- 40,000 ብር ሎት9 ፡- ለእያንዳንዱ መኪኖች 15,000 ብር ሎት10፡- 70,000 ብር ሎት11፡- 20,000 ሎት12 ፡ 25,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡የሚያስይዙትም የዋስትና አይነት ቢያንስ ለ90 ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት።
9. የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆየውም ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ 45 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
10. በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ፤ጨረታ ሰነዱ በፍሉድ ከተነካ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
11. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል።
12. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
13. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ኮፒዎች ላይ በመጠቀም እና የጨረታ ሃሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ በጥንቃቄ በ2 ፖስታ ለየብቻ በማሸግ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚሸጠውን የጨረታ መመሪያመመልከት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በግንባር በመቅረብ ወይም ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 116 01 99/54 ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በሕዝብ በዓላት ቀን ከሆነ ወደፊት ባለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ናሙና ላስቀመጠላቸው እቃዎች ብቻ በናሙናው መሰረት ያሸነፉትን እቃ ማቅረብ አለባቸው።
በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ወረኢሉ
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wereilu Woreda F/E/D/B
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Nov 12, 2026)
- Posted at: 2026-11-12T09:04:28.000Z
- Source: Qelal Tenders