Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 6 ት/ጽ/ቤት የቤኬ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ግብአቶችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክ ከተማ በወረዳ 6 ት/ጽ/ቤት የቤኬ ቅድመ 1ኛ ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማለትም

ሎት 1፣ የደንብ ልብስ፣ ሎት 2, የቢሮ እቃዎች፣ ሎት3, የህትመት ስራዎች ፤ሎት4, አላቂ የህክምና እቃዎች፣ ሎት5, የትምህርት እቃዎች፣ ሎት6. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን ፣ ሎት 8, ፈርኒቸሮች እና ሎት 9, ፕላንት ማሽነሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤

1. ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸዉ፤

2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣

3. የዘመኑን ግብር ስለመከፍላቸው ከመሚለከተዉ አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት/ ያላቸዉ።

6. በድህረ ገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጃዉ ክፍል /AGP/ የተመዘገቡ መሆን አላባቸዉ።

1. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በመለየት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቹ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በየሎቱ በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ከኦሪጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ ማቅረብ አለበት።

ሎት 1, ለደንብ ልብስ

 

25,000 ብር

 

 

ሎት 6, ለጽዳት እቃዎች

 

25,000 ብር

 

ሎት 2 ለቢሮ እቃዎች ሎት

 

25,000 ብር

 

 

ሎት 7, ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች

 

40,000 ብር

 

ሎት 3 ለህትመት ስራዎች

 

10,000 ብር

 

 

ሎት 8, ለፈርኒቸሮች

 

50,000 ብር

 

ሎት.4.አላቂ የህከምና እቃዎች

 

25,000ብር

 

 

ሎት 9, ለፕላንት ማሽነሪዎች

 

50,000 ብር

 

ሎት.5 ለትምህርት እቃዎች

 

25,000 ብር

 

 

 

 

ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጃዉን የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከ ት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ ክፍል በየሎቱ የማይመለስ 200ብር (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በግልፅ በመሙላት ለዚሁ በተዘገጀዉ ሳጥን ዉስጥ ኮፒና ኦሪጂናል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለባቸዉ።

1.1 ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 መጫረት ወይም መርጠዉ አንዱን ወይም ሁለቱን መጫረት ይችላሉ፤ ነገርግን ከያንዳነዱ ሎት እቃዎች መራርጠው ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።

1.2 የጨረታዉ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ3፡30 (ሶስት ሰዓት ተኩል) ታሸጎ በእለቱ በ4፡00 (አራት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ ህጋዊ ወኪል/ ያለመገኝት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽኖ አይኖረዉም።

1.3 የጨረታ አሸናፊ ለአሸነፈዉ እቃ 10 ፐርሰንት ዉል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።

1.4 ተጫራቾች ከሎት1- ሎት7 ላሉት እቃዎች ናሙና ጨረታው ከመታሸጉበፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ሎት8 እና 9 እስፔስፊኬሽን ያለው ፎቶ ቢሆን ይመረጣል።

1.5 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በትራንስፖርት በማጓጓዝ የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማስገባት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

1.6 በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቡት እቃ በናሙናው መሰረት ካልሆነ ተቀባይነት የለዉም።

1.7 በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለዉም።

2. ቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ የጽዳት ዕቃ፤ የትምህርት እቃዎች፣የቢሮ እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ፕላንት ማሽነሪ፣ፈርኒቸሮችና፣ የላብራቶሪ ግብዓቶች፣ የህክምና እቃዎች፣ ህትመት እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በሠንጠረዥ በቀረበዉ መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሞልታችሁ በማስገባት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

2.1 ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የት/ቤቱ አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቦሌ አራብሳ ልዩ ስሙ ከሰፈራ አደባባይ ወደ ባዕታ ማርያም በሚወስደው መንገድ ሳይት አምስት ኮንዶሚንየም መሀል መሆኑን እንገልፃለን።

የቤኬ ቅድመ 1ኛ ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): የጨረታዉ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ3፡30
  • Bid opening: 2026-11-25 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታዉ ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን በ4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የቤኬ ቅድመ 1ኛ እና አንደኛ ደ/ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T07:34:34.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders