Equipment and Accessories
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው እቃዎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ-08/2019 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው የእይታ መሳርያ(መነፅር)፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል(የቤት ክዳን ቆርቆሮ)፣ አዳዲስ አልባሳት፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላ።
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
3. በግልፅ ጨረታ ላይ የወጡትን ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በብሄራዊ መታወቂያ ብቻ የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
4.የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-8፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።
5. የጨረታው በጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታ አይነት |
በጋዜጣ የታተመበ ቀን |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት |
ስልክ ቁጥር |
|
1 |
ኮንስትራክሽን ማቴሪያል |
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
2 |
የእይታ መሳርያ (መነፅር) |
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
3 |
አዳዲስ አልባሳት
|
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
4 |
ኤሌክትሮኒክስ |
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
5 |
ተሸከርካሪ መለዋወጫ
|
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
6 |
ኮንስትራክሽን ማቴሪያል (የቤት ክዳን ቆርቆሮ) |
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
|
7 |
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች |
ግልፅ |
04/3/2019 |
11/3/2019 |
4:00 |
4:30 |
022 111 8429 022 211 8925 |
6. በግልፅ ጨረታ ሽያጭ ላይ የእቃዎቹ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች አስመጪ ወይም የአስመጪ ቤተሰብ መሳተፍ አይችሉም። ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።
7. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
8. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ እንዲሁም ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች መስሪያ ቤቱ አዳማ ቆርቆሮ አከባቢ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 5 የሚገኙ ሲሆን ለግልፅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
11. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።
የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ጉምሩክ መጋዘን የስራ ሂደት
ስልክ ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-20 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የሰጡትን ዋጋ 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
- Posted at: 2026-11-13T08:26:47.000Z
- Source: Qelal Tenders