Pumps, Motors and Compressors

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ (Supply of External wet type fire hydrant and Fire hydrant cabinets) እንዲሁም (Supply, Fix, Test and Commissioning Fire fighting Pumps) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/BM/164/2026 እና DCE/SF/165/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply of External wet type fire hydrant and Fire hydrant cabinets Supply, Fix, Test and Commissioning Fire fighting Pumps ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የዕቃውን ዓይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

1

Supply of External wet type fire hydrant and Fire hydrant cabinet

ጎፋ አፓርትመንት ፕሮጀክት

DCE/BM/164/ 2026

ህዳር 16/2019ዓ.ም 8፡00 ሰዓት

ህዳር 16/2019 ዓ.ም 8፡15 ሰዓት

50,000.00

 

2

Supply and Fix Fire Fighting Pumps

ጎፋ አፓርትመንት ፕሮጀክት

DCE/ SF/165/2026

ህዳር 16/2019 8፡15 ሰዓት

ህዳር 16/2019 ዓ.ም  ዓ.ም 8፡30 ሰዓት

100,000.00

 

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ከሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ…ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሠንጠዥ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ  0114-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ [email protected]

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

ፖ.ሳ.ቁ 3414 4hh ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ  


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 14:15
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-11-25 14:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer's registered address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T08:48:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders