Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዮ ጃፓን ህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የኢትዮ ጃፓን ህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 001/2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽዳት እቃ የስፖርት ትጥቆች አላቂ የህክምና እቃዎች፣ የትም/እቃዎች፣አላቂ የቢሮ እቃዎች ቃሚ እቃዎች ወዘተ... በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1.በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስከር ወረቀት ያላቸው። ተጫራቾች ሀጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፡ቲን ነምበር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል ።
2. ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ከዓይነቱ አንድ አንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ የቀረቡት ናሙናዎች የተሸናፊ ሲመለስ የአሸናፊ ተጫራቾች ናሙና ዕቃውን እስከሚያቀርቡ ድረስ አይመለስም።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ/ብር በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኢጃ/ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻል አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- ሎት (lot) 1. (40000 ብር) ሎት (lot) 2(14000) 3. ሎት3 (lot) (ብር 4000) 4. ሎት4 (lot) (ብር 1000) ሎት (lot) 5 (22000) 6.ሎት(lot) 6 (ብር 40000) 7.ሎት (lot)7 (ብር 8000) ሎት(lot) 8 _ (ብር 2000 ) 10.ሎት(lot) 10 (ብር 10000 )
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒውን የጨረታ ቁጥር እና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኢንቨሎፕ ላይ በመጻፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኢ/ጃ ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11 ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ኢጃ/ህ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ : ላይ : የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
9. ተቋሙ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው specification መሆናቸው ጥራት ዋስትና አጠቃሎ ማቅረብ ግምት ውስጥ ይገባል።
10. ተቋሙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
11. የጥቃቅንና አነስተኛ የሆኑ ተጫራቾች አምራች እና በሀገር ውስጥ ምርት መወዳደር ይችላሉ።
12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
13. ማንኛውም ተጫራቾች በሳምፕሉ ላይ የራሱን ስም (የድርጅቱን ማህተም)የመሳሰሉትን የጻፈ (ማህተም ያደረገ) ከውድድሩ ይሰረዛል።
በስልክ ቁጥር፡- 011 434 6843/6914 ፖስታ ሣጥን ቁጥር 540
የኢትዮ-ጃፓን ህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ/ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-11-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን 4፡30 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Japan Hidase Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
- Posted at: 2026-11-13T08:10:43.000Z
- Source: Qelal Tenders