Materials

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 001/2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ግብዓቶች አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 001/2019 በጀት ዓመት አንደኛ ዙር በግልፅ ጨረታ የተለያዩ ግብዓቶች አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡

1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ሰነድ ከአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 4 ኪሎ ግንፍሌ ድልድይ ከፍ ብሎ ወረዳ 7 የግዥ ቡድን ከካፍቴሪያ ጎን ምድር ላይ በሚገኘው ቢሮ በአካል በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo)

  • ለሎት1. የስልጠና እቃዎች……………………………10,000.00 ብር
  • ለሎት-2. የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች………………….10,000.00 ብር
  • ለሎት 3. የጽዳት እቃ……………………………………..….10,000.00 ብር
  • ለሎት-4. የደንብ ልብስ……………………………………….10,000.00 ብር
  • ለሎት 5. የህትመት ስራዎች……………………………..……5,000.00 ብር
  • ለሎት-6. የዴኬር ወይም የህጻናት ማቆያ እቃዎች………5,000.00 ብር
  • ለሎት-7. የህንጻ ጥገና አገልግሎት እቃዎች……………..5,000,00 ብር
  • ለሎት-8. የመኪና እቃዎች………………………………….10,000,00 ብር

በባንክ በተረጋገጠ Certified Payment Order (CPO) ብቻ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ ቫትን ባካተተ መልኩ መሙላት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት በመመደብ የጉልበት ሰራተኛ ጫኝ እና አውራጅ በማቅረብ ለኮሌጁ ንብረት ግምጃ ቤት ያስረክባሉ።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ በምርመራ ላይ በተቀመጠው መሆን አለበት።

9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ከአሸናፊው ድርጅት ጋር በውል ላይ በተቀመጠው ብዛት ላይ ዋጋ ሳይቀየር 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።

ጥብቅ ማሳሰቢያ፡- የጨረታውን ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ለወደፊቱ በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ታግዶ ያስያዘው ዋስትና ይወረሳል።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ በሰነዱ ምርመራ ላይ በተጠቀሰው መሰረት በእስፒክ ወይም ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ማቅረብ አለበት።

አድራሻ፡- አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ግንፍሌ ድልድይ ከፍ ብሎ ወረዳ-7

ስልክ ቁጥር፡- 0999 919 578

አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-25 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Manufacturing College
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T08:11:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders