Generators

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ልዩ የተለያዩ ቀላል ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ያገለገሉ ጀነሬተር እና ታወር ላይት መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/0016/2019

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

  • ልዩ የተለያዩ ቀላል ተሽከርካሪዎች ማሽነሪዎች
  • ያገለገሉ ጀነሬተር እና ታወር ላይት መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡

  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ…ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ30 (ሠላሳ ቀናት) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር

አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ  0114-42-22-70/71/72

E-mail አድራሻ [email protected] 

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com 

ፓ.ሳ.ቁ 3414

ፋክስቁ.0114-40-04-71/0114-42-07-46

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-12-14
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Bid opening: 2026-12-14 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer's registered address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T08:45:05.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders