Vehicle and Machinery Sale
የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ መዋጮ ዕዳ ለማስከበር ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል
Description
በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የጡረታ
መዋጮ ዕዳ ለማስከበር የወጣ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ስማቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅቶች ከሠራኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ማድረግ ባለመቻላቸው የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 በተሠጠው ስልጣን መሠረት የድርጅቶቹን ሃብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳው እንዲሰበሰብ ተወሰኗል፡፡በዚሁ መሠረት
|
ተራ ቁጥር |
ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው የሚፈለግበት ድርጅት ሥም |
ከድርጅቱ የሚፈለገው የጡረታ መዋጮ ዕዳ መጠን |
የተሽከርካሪው ወይም የማሺነሪው ሠሌዳ ቁጥር |
የድርጅቱ ሃብት የሚገኝበት አድራሻ
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
|
1 |
ኤል አሰብ ጄኔራል ትራንስፖርት ኤንድ ኮንስትራክሽን ኢስቴብ |
27,110,777.29
|
የሠሌዳ ቁጥር ሥከ -cs-0636 |
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምእራብ ሐረርጌ ዞን ባዴሳ ከተማ |
37,082,909.90
|
|
2 |
ሩሜ አግሮ ኢንደስትሪ ኃ/የተ/የግ ማ |
7,230,029.01
|
የሠሌዳ ቁጥር አአ-03-A22792 |
አዲስ አበባ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት |
757,336.71
|
|
3 |
ኤልሻዳይ ፊሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን |
6,595,375.93
|
የሠሌዳ ቁጥር አአ-05-02606 |
አዲስ አበባ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መስሪያ ቤት |
683,948.25
|
- ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬት ወይም ከህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት እንዲሁም ከሠአት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ4፡15 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹ ወይም ማሺነሪዎቹን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባለት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሃብቱን መረከብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
- ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ህጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ።
- አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111570333
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-12-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-12-02 10:15
- Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡15 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: FDRE Private Organizations Employees Social Security Agency
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
- Posted at: 2026-11-14T08:09:01.000Z
- Source: Qelal Tenders