Equipment and Accessories

የደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የደ/ምዕ/ኢት/ሕ/ክል/መ/ጠቅ/ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለፍ/ቤቱ ሥራ አገ/ት ዕቃዎችን በተለያዬ ሎት ከህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1 የኔትወርክ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 2 አይሲቲ መለዋወጫ እቃዎች፤
  • ሎት 3 የቢሮ ፈርኒቸር
  • ሎት 4 የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች

በዚሁ መሠረት ከተጫራቾች ተሟልቶ መቅረብ ያለበት፤ 

1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ እና የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት

2. የቲን ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ

3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል

4. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በተጠቀሰው ስፔስፍኬሽን መሠረት በማሟላት በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው እስቶር ለማቅረብ የሚችሉ

5. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕ/ኢ/ህ/ክ/ገቢዎች ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000513995777 ላይ በማስገባትና የገቢ ድረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከጠቅላይ ፍ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት መውሰድ የሚችሉ

6. የጨረታው አየር ላይ ቆይታ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ 16ኛው ቀን በ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ 8፡00 ሰዓት የሚከፈት ሆኖ የመክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል።

7. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት የተለያዬ ሲሆን ሎት 1. 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 2. 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 3 እና 4 ለእያንዳንዳቸው 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ግልፅ የሆነ ቴክኒካል መግለጫ ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ /በድርጅቱ ፕሮፎርማ ማቅረብያ ከሆነ በመ/ቤቱ የተዘጋጀው ቅደም-ተከተል ሳይዛባ / ዋጋ በመሙላት በአንድ ኮፒ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን የጨረታው ቀንና ሰዓት ከማለቁ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

10. የሚከፈትበት ቦታ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ክፍያ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አንደኛ ፎቅ ላይ ነው

11. ተጫራቾች የተፈለገውን የእቃ ጥራት ወይም ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

12. የተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 135 1716
የደ/ምዕ/ኢት / ሕ / ክል/ መ / ጠቅ / ፍ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-30
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ 16ኛው ቀን በ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-30 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታው ሳጥን በ 16ኛው ቀን በ 8፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: South West Region Supreme Court
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
  • Posted at: 2026-11-14T08:15:17.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders