Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የደብረብርሃን ከተማ ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን ከተማ ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 3 የጽዳት እቃ
  • ሎት 4 የእንስሳት መድሃኒት
  • ሎት 5 የእንስሳት የህክምና መሳሪያ
  • ሎት 6 የተሽከርካሪ ጎማ
  • ሎት 7 የተማሪ ምገባ አቅርቦት
  • ሎት 8 የከተማ ባስ

በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የግዥውን ዓይነት፣ መጠንና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብና በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

  • ለጽህፈት መሳሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣
  • ለኤሌክትሮኒክ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣
  • ለጽዳት እቃ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣
  • ለእንስሳት መድሃኒት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣
  • ለእንስሳት የህክምና መሳሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣
  • ለተሽከርካሪ ጎማ ብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) ፣
  • ለተማሪ ምገባ ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) እና
  • ለከተማ ባስ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በደብረብርሃን ከተማ አስተዳር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ይውላል። በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ቀን 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ አለት 4፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፣ ታዛቢዎች እና የውስጥ ኦዲተሮች በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ተጫራቾች በአከፋፈቱ ስነስርኣት ላይ ባለመገኘታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።

9. መስሪያ ቤቱ ውድድሩን የሚያካሒደው በሎት ጥቅል ነው።

10. ተጫራቾች በቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ በነጠላ ወይም ጠቅላላ ድምር ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል። በተጨማሪም የቀረበውን የጨረታ ሰነድ ጠቅላላ ድምር ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።

11. የግዥ ፈጻሚ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12 የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

13. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደብርብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 637 56 10 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-23
  • Bid closing time: 10:05
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Berhan City Administration Finance Department
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
  • Posted at: 2026-11-14T08:27:57.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders