Water System Installation

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለእስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በተመደበው በጀት መሰረት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም መስፈርቱን የሚያሟሉ በውሃ ነክ ስራዎች ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

የሥራው ዓይነት፡- ለእስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ስራ

የታተመው ህዳር 07 2019 ዓ.ም

የግዥው መለያ ቁጥር: አብክመ/ውኢቢ/ ብግጨ /ግስግ/ቁጥር-01/2019

የግዥ ዘዴ - ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለእስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በተመደበው በጀት መሰረት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም መስፈርቱን የሚያሟሉ በውሃ ነክ ስራዎች ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

ተ.ቁ

የፕሮጀክት ስም

ወረዳ

ዞን

ፕሮጀክቱ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር

1

እስታይሽ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት

ጋዞ

በሰ/ወሎ

ግንባታ፤ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ስራ

1,500,000.00

1. የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሰርቲፊኬት/ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በዘመኑ የታደሰ እና ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከዚህ በላይ በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ (CPO)፤በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ (Amhara National Regional State Bureau of Water and Energy) ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናሻያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴከነካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፋይናሻያል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች በማሸግ በድምሩ ስድስት ለየብቻ በታሸገ ፖስታዎች እና ቴክነካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች የታሸጉ ፖስታዎች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ፋይናሻያል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፖስታዎችን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የግዢውን _ ስም በመጻፋ በውኃና ኢነርጅ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. የስርዝ ድልዝ ወይም የተፋቀ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

9. ጨረታው መዝጊያ ቀን 07/04/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን ጨረታው 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በዚህ ግዥ ላይ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ የተቀመጡት መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

12.ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥሮች +251 582-26-24-60/ +251 582-20-08-55 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር +251 582-26-24-61 በመላክ ወይም ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፡፡

ውኃና ኢነርጂ ቢሮ

ባሕር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-12-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-12-16 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Water and Energy Bureau
  • Bid bond: 1,500,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T11:16:10.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders