Water Construction

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት (Packed System) በተመደበው በጀት መሠረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

የሥራው ዓይነት- ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ (Packed System)

የታተመው፤ ኅዳር 7/2019

የግዥው መለያ ቁጥር- አብክመ/ውኢቢ / ብግጨ / ግስግ/ ቁጥር-02/2019

የግዥ ዘዴ፤ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት (Packed System) በተመደበው በጀት መሠረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም መስፈርቱን የሚያሟሉ በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ብቁ የሆናችሁ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

ተ.ቁ

የፕሮጀክቱ ስም

ወረዳ

ዞን

ፕሮጀክቱ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር

1

ወይን ውኃ ከተማ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት (Packed System)

ቢቡኝ

ምስ/ጎጃም

ግንባታ፤ የቧንቧ፣ መገጣጠሚያና ኤሌክትሮ ሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ሥራ (Packed System)

1,800,000.00

በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

1. በውሃ ነክ ሥራዎች ተቋራጭነት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት /ሰርቲፊኬት/ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ

2. በዘመኑ የታደሰ እና ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 23 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከዚህ በላይ በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO)፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃና ኢነርጂ ቢሮ (Amhara National Regional State Bureau of Water and Energy) ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል እና ፋይናሻያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክነካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፋይናሽያል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች በማሸግ በድምሩ ስድስት ለየብቻ በታሸገ ፖስታዎች እና ቴክነካል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች የታሸጉ ፖስታዎች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ፋይናሽያል ዋና እና ሁለት ቅጅዎች ፖስታዎችን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሎት የግዢውን ስም በመጻፋ በውኃና ኢነርጂ በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. የስርዝ ድልዝ ወይም የተፋቀ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

9. ጨረታው መዝጊያ ቀን 07/4/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን ጨረታው 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃ ተቋማት ግንባታ ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ ቀን በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በዚህ ግዥ ላይ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ የተቀመጡት መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

12. ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥሮች +251 582-26-24-60 / +251 582-20-08-55/ በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር +251 582-26-24 61 በመላክ ወይም ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት

ውኃና ኢነርጂ ቢሮ

ባሕር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-12-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-12-16 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Water and Energy Bureau
  • Bid bond: 1,800,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T11:15:51.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders