Freight Transport
በአብክመ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የአንድነት የዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የአንድነት የዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃወችና የአገልግሎት ግዥዎች በሎት ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 01. የፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ ግዥ፣ ሎት 02. የምርጥ ዘር የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ሎት 03. የዘር ማበጠሪያ ማሽን ቁሳቁስ ግዥ፣ ሎት 04. የፅዳት ዕቃወች ግዥ
ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. የዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን ናምበር) ማቅረብ የሚችሉ።
3. ከትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ውጭ ለሆኑት የግዥው መጠን ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ከታወቀ ባንክ በጥሬው የባንክ ጋራንቲ (ቢል ቦንድ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃ ግዥ ወይም የአገልግሎት ግዥ ዓይነቶች ዝርዝር መገለጫ ስፔፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
7. ተጫራቾች በየሎቱ የወጣውን ጨረታ በዕየሎቱ አካቶ መሙላት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል አንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ኃ/የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 ሀቂቃ ህንፃ የገበያ ማዕከል (ቀበሌ 14 ከሚገኘው ኖክ ማደያ ፊትለፊት ከሚገኘው ህንፃ) 1ኛ ፎቅ ላይ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 251 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ጨረታው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ከህዳር 07 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ይሆናል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሞልተው በሚመለከተው አካል ተፈርሞበት፣በፖስታ/ኢንበሎፕ/ ከታሸገ በኋላ ፖስታው ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም በማድረግ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።የቀረበው የጨረታ ሰነድ ሳጥኑ ማስገባት ባይችል የጨረታ ኮሚቴው ፈርሞ ይቀበላል፡፡
10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም። የጨረታ መክፈቻው ቀን ካላንደር ቢሆን የመክፈጫ ቀኑ ወደ ሚቀጥለው ቀን ይሸጋገራል፡፡
11. በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈበት 10በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል።ስለሆነም በዩኒየኑ በስራ ጫና ምክንያት ከአልሆነ በስተቀር በ5 ቀን ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበያ ሁለት በመቶ ውርስ ይደረጋል።
12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ዩኒዬኑ ባወጣው የጨረታ መጠን በየሎቱ መጨመርም ሆነ መቀነስ ሊኖር ይችላል፡፡
14. ዩኒየኑ አሸናፊውን የሚለየው ከትራንስፖርት ጨረታ እና ከፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ጥሬ እቃ አቅርቦት ጨረታ ውጭ በጠቅላላ ዋጋ ድምር ውጤት ይሆናል፡፡ ከላይ ያልተገለፁ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒዬኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል።
15. ለበለጠ መረጃ ለማገኘት፡- 0930709926/ 0979261356/ 0918218740/ 0918987382 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
አንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-11-27 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: አንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒዩን ኃ.የተ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:16:57.000Z
- Source: Qelal Tenders