Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የፅህፈት መሳሪያ እና የፕሪንተር ቀለም፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቆሎ፣ የታሸገ ውሃ፣ ኩኪስ እና ቡና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ኢፕድ 0013/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የፅዳትና የፅህፈትመሳርያና የፕሪንተር ቀለም ቆሎ የታሸገ ውሃ ኩኪስ እና ቡና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት ፡-1 የፅህፈት መሳሪያ እና የፕሪንተር ቀለም
  • ሎት፡-2 የፅዳት ዕቃዎች
  • በሎት ፣-3 ቆሎ የታሸገ ውሃ ኩኪስ እና ቡና

በዚህም መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስከር ወረቀት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመዉሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በአቅርቦት መምርያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚዉል ብር

  • ለሎት 1፡- 20,000 (ሃያ ሺህ )
  • ለሎት 2፡- 15,000 (አስራ አምስት ሺህ )
  • ለሎት 3፡- 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸዉ አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡

4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ይከፈታል ፡ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ስልክ ቁጥር 0111 569 869

ኢ ሜይል [email protected]

አድራሻ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer's registered address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T10:08:34.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders