Textile, Garments and Uniforms
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2019
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዢ የደንብ ልብስ ስፌት እና የስፖርት ትጥቅ ሎት 2 የፅዳት እቃ ሎት3፡- የህክምና ዕቃ የመጀመሪያ እርዳታ የሚውል ሎት 4 የላቦራቶሪ እቃዎች ሎት 5 የትምህርት መርጃ መሳሪያ ሎት 6፡ የፅህፈት መሳሪያ ሎት 7፡-የቋሚ እቃ ሎት 8፡-የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሎት 9፡- የህትመት ስራዎች ሎት 10፡ የህንፃ እና ተገጣጣሚ እቃዎች ጥገና እነዚህን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በየዘርፉ የተሰማሩትን ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ማቅረብ የሚችሉ
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች የተዘጋጀው ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት ሎት 1፡- 4,000 ብር ሎት2፡- 6,000 ብር ሎት3፡- 400 ብር ሎት4፡ 2,500ብር ሎት5፡- 2,500ብር ሎት 6፡ 5,000ብር ሎት 7፡- 8,540ብር ሎት 8፡-500ብር ሎት 9፡ 900ብር ሎት 10፡ 3000 ብር ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በቀለም አምባቅ/አ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በማስያዝ ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ ያልያስያዘ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በት/ቤቱ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ኮፒውን ለዚህ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
8. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ |ተጫራች| ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
10. የጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚያገኙት ባመረተው ምርት እና በምርቱ ላይ እሴት በጨመሩት ብቻ ሲሆን ሌሎች እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው CPO አስይዘው ይወዳደራሉ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ት/ቤቱ የዕቃዎቹን ብዛት 20% የመጨመር የመቀነስ/ መብቱ የጠበቀ ነው።
13. የጨረታው አሸናፊ መሆንዎ ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ካሸነፈበት የጨረታ ዋጋ 10% CPO በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 9 ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን
ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ
ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ
ስልክ 011 2 30 41 55
የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-27
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-28 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kelem Ameba Primary & Middle School
- Buyer's registered address: ሩፋኤል ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
- Posted at: 2026-11-17T13:52:32.000Z
- Source: Qelal Tenders