Textile, Garments and Uniforms
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ ማለትም የቆዳ ጫማ፣ የሴፍቲ ቆዳ ጫማ፣ የፖሊስተር ጨርቅ ሆኖ ሰማያዊ ከለር ቱታና ገዋን፣ ሸሚዝ፣ 1ኛ ደረጃ ቴትረን ጨርቅ ሆኖ ኮትና ሱሪ፣ ሱሪ፣ ቀሚስ፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰፋት ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ የሰራተኛ የደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ ማለትም የቆዳ ጫማ፣ የሴፍቲ ቆዳ ጫማ፣ የፖሊስተር ጨርቅ ሆኖ ሰማያዊ ከለር ቱታና ገዋን፣ ሸሚዝ፣ 1ኛ ደረጃ ቴትረን ጨርቅ ሆኖ ኮትና ሱሪ፣ ሱሪ፣ ቀሚስ፣ ከረቫት፣ ኮፊያና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሰፋት⁄ ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ/ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይችላሉ። እንደዚሁም ለሚሳተፉበት የአልባሳት አይነት ለጥራት ሙከራ የሚሆን ናሙና አስቀድሞ ወይም ጨረታው በሚከፈትበት እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ በድርጅቱ የግዥ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አድራሻ ወይም በግዥ ክፍል ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ናሙና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ካልሆነ በዋጋ ዝቅተኛ ቢሆንም እንኳን በጥራት ምዘና የሚሰረዝ ይሆናል።
8. በአልባሳት ላይ የሚሳተፍ እና አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨርቅ ከራሱ ሆኖ ከማህበሩ ቢሮ በመምጣትና የሰራተኞቹን ልኬት በመውሰድ በትክክል ሰፍቶ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።
9. በአልባሳት ላይ ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ስለስፌቱ አይነት፣ ጥራትና የማስረከቢያ ጊዜና የክፍያ ሁኔታ አስቀድሞ ውል መፈረም ይኖርበታል።
10. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉምሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር:- 01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ፡- 0115 51 86 96
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-12-01
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-01 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Printing P.L.C.
- Buyer's registered address: ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
- Posted at: 2026-11-17T10:57:29.000Z
- Source: Qelal Tenders