Stationery

በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለ2ተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለ2ተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የተወዳዳሪዎች መመሪያ፡-

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

 2. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000063129848 ገቢ በማድረግ ፡፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ጉዳይ ቢሮ ቁጥር WW.08 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም፣ፊርማና አድራሻ በትክክል ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ጨረታ ላይ ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ የስራ ሰዓት ይሆናል።

7. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 ( ሰላሳ ሺህ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.PO.) ማቅረብ ይኖርበታል።

8. ተጫራቾች ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ያዘጋጀውን የእቃ ናሙና በማየት ዋጋ በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

10. አሸናፊው ተጫራች የሠራተኞች የደንብ ልብስ መ/ቤቱ ባዘጋጀው ናሙና መስረት አይቶ ዋጋ ቤቱ ባዘጋጀው መና መስረት አይ በመሙላት መወዳደር ሲኖርባቸው፣ ኤሌክትሮኒክስን በተመለከተ መለያ ቁጥሩን አስመዝግቦ በሚመደበው ባለሙያ የእቃዎች ጥራትና ብቃት ተረጋግጦ ገቢ ከተደረገ በኋላ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።

11. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫት ተጨምሮ መሞላት አለባቸው።

12. ጽ/ቤቱ የእቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

13. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0915 839 978/0915 804 892 ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-04 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Zone Chole Woreda FEDB
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T11:37:57.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders