Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር በአቢሻገር ክ/ከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚሆን የተለያዩ እቃዎችን ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር በአቢሻገር ክ/ከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት 02 የፅዳት እቃዎች ሎት 03 የደንብ ልብስ 04 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በቀን 04/02/2019 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ በዘመኑ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላችው።
2. የግዢ መጠኑ ከብር 500000/አምስት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ ተጫራቾቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-7 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅር አለባቸው።
4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በ CPO ብቻ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ጸንቶ ይቆያል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት በመክፈል ከ04/03/2019 እስከ 18/03/2019 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰአት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይቻላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶች ኦርጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ04/03/2019 እስከ 18/03/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑ በቀን 19/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል። ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በአል ከሆነና የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰአት የሚከፈት ሆናል።
8. አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች በክፍለ ከተማዉ ሳምፕል የሚያቀርብ በመሆኑ ሳምፕሉን በጥንቃቄ በማየት ዕቃዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ችን ማቅረ
9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኝ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያገጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ጨረታ መክፈቻ 5/አምስት / ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914 358 368 / 0910 193 141 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
11. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውድድር ውጭ የስደርጋል።
12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ45 ቀናት ይሆናል።
13. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቶች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪየ ቤቱ ግዥ የማያሳትፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል።
14. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
15. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን አቢሻገርክፍለ ከተማ አስተዳደር ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ የጠበቅበታል።
16. ክፍለ ከተማዉ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊለም ሆን ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ኮምቦልቻ
Tender details
- Deadline: 2026-11-28
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-28 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: አቢሻገር ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን
- Bid bond: 1% ለእያንዳንዳቸው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
- Posted at: 2026-11-17T10:26:35.000Z
- Source: Qelal Tenders