Construction Machinery
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ትራክ ኪራይ በቁርጥ ዋጋ ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ኮንስትራክሽን ማሽነሪ እና ትራክ ኪራይ አገልግሎት በቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2019 በጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ትራክ ኪራይ በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርች ከሚያሟሉ አከራዮች ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
|
S.No |
Description |
Quantity |
የማሽኑ አቅም |
ዝቅተኛ የስሪት ዘመን |
የውል ዋጋ በሰዓት ተ.እ.ታ እና ነዳጅን ጨምሮ |
|
1 |
Chain Excavator (Bucket) |
31 |
≥1.6M* Heaped and≥ 200 Hp |
> 2015 GC |
8,798.44 |
|
2 |
Water truks |
13 |
≥13000 litter |
> 2013 GC |
4,686.40 |
|
3 |
Backhoe Loader |
12 |
≥1M3 Front Bucket capacity, ≥ 0.25 Backhoe bucket capacity ≥ 90 Hp |
> 2010 GC |
3,654.72 |
|
4 |
Wheel loader |
20 |
>3M3 Bucket capacity and ≥ 180 Hp |
> 2015 GC |
4,700.00 |
|
5 |
Dozer |
6 |
≥300 Hp |
> 2013 GC |
11,750.76 |
|
6 |
Single drum roller |
13 |
≥ 16 Ton |
> 2008 GC |
5,571.36 |
|
7 |
Motor Grader |
10 |
≥ 140 Hp |
> 2012 GC |
8,143.24 |
|
8 |
Chain Excavator (Jack Hammer) |
13 |
> 200 Hp, min. operating weight shall be ≥2500 kg and min. impact rate shall be ≥ 350 bpm |
> 2015 GC |
10,362.04 |
|
9 |
Wheel Excavator |
8 |
> 1M3 Bucket capacity and ≥ 135 Hp |
> 2003 GC |
8,151.00 |
|
10 |
Double drum roller |
3 |
4 Ton |
> 2008 GC |
4,398.30 |
|
11 |
Asphalt Distributor |
1 |
> 7000 litter |
> 2010 GC |
9,522.17 |
|
12 |
High-Bed |
1 |
≥ 50Ton |
> 2010 GC |
7,376.00 |
|
13 |
Mixer truck |
5 |
Minimum =7M3 net |
> 2012 GC |
3,927.00 |
|
14 |
Pneumatic Roller |
4 |
> 12 Ton( Un ballasted) |
> 2003 GC |
6,037.73 |
|
15 |
Low-bed |
2 |
> 50 Ton |
> 2010 GC |
7,376.00 |
1. አከራይ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፤ያገልግሎት ጊዜው ያላበቃ የብቃት ማረጋገጫ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. መመዝገብ የሚችሉት የተሽከርካሪው ባለቤት ወይም በስማቸው ማሽነሪውን ማከራየት እንደሚችሉ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ህጋዊ ውክልና የሚያቀርቡ ብቻ ናቸው፡፡
4. አከራይ እንዳመጣጣቸው ቅደመ ተከተል ተመዝግበው በቅድም ተከተሉ መሰረት ለስራው ይጠራሉ፡፡
5. ለኪራይ የቀረበው የኮንስትራክሽን ማሽነሪ የቴክኒክ ይዘት ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት ስለመሆኑ የባለስልጣን መ/ቤቱ የመሳሪያ አቅርቦት አስተዳደርና ጥገና ዳይሬክቶሬት እያረጋገጠ ስምሪት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
6. የነዳጅ ዋጋ በመንግስት ውሳኔ ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ባለስልጣን መ/ቤቱ የዋጋ ማስተካከያ በውሉ ላይ በሚገለጸው ቀመር መሰረት ማስተካከያ ያደርጋል፡፡
7. አከራዮች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ለምዝገባ የሚስፈልጉትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ማሽነሪዎች በአግባቡ የሚሰራ GPS መከታተያ ስርዓት የተገጠመላቸው መሆን አለባቸው
9. የGPS ቁጥጥር ሂደቱ በተከራይ በኩል የሚፈፀም ይሆናል፣የቁጥጥርና የክትትል ሂደቱን ለማከናወን አከራይ አስፈላጊውን የGPS user Account በቴክኒክ ምርመራ ወቅት ለባለስልጣን መ/ቤቱ ተወካይ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
10. በኪራይ የሚገቡ ማሽነሪዎች ሳይት ላይ በስራ ላይም ሆነ ያለስራ በሚቆሙበት ወቅት የማሽሪዎቹን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነቱ የአቅራቢው ነው፡፡
11. ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመስሪያ ቤቱ ጋር በነበራቸው የቀድሞው ውሎች የምርታማነት ችግር ያላባቸው ማሽኖችና ትራኮች እንዲሁም የአፈጻጸም ችግር ኖሮባቸው በተሰጣቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤዎች ተገቢውን ማስተካከያ ያላደረጉ አቅራቢዎች በዚህ የኪራይ ጥሪ ተሳታፊ አይደረጉም፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ የኪራይ አገልግሎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 0113-72-28-25 / 0113-72-00-47
ፑሽኪን አደባባይ ሳርቤት
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-12-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Bid opening: 2026-12-01 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
- Buyer's registered address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
- Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
- Posted at: 2026-11-17T10:21:31.000Z
- Source: Qelal Tenders