Stationery
የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች እና የማሽን ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለዳባት ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ
- የጽህፈት መሳሪያዎች እና
- የማሽን ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የ2019 የንግድ ፈቃድ ያደሱ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- የሚሞት ጠቅላላ ዋጋ ከ500‚000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 - 6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩት ዋጋ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 10 ቀናት ከህዳር 7/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 16/2019 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ፈቃዱን ይዞ መምጣት አለበት፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ብሄራዊ በዓል እና ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀናት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ ህዳር 17/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት (በጥቅል) ድምር ነው፡፡
የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-26 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Dabat City Administration F/E/D/Bureau
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:03:07.000Z
- Source: Qelal Tenders