Equipment and Accessories

በአብክመ የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ካላስተር ማዕከል በ2019 ዓ.ም ለአገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ካላስተር ማዕከል በ2019 ዓ.ም ለአገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 2. የቋሚ እቃዎች፣
  • ሎት 3. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 4.የጽዳት እቃዎችና ሌሎች አላቂ፣
  • ሎት 5.የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 6. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ሎት 7. የህትመት እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል ፡፡

 የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በስራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የሚችሉ።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተ ፍኬት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በወ/መ/ሙ/ብ/ማ/ክ/ማ ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች እሪጂናል ስለመሆናቸው በሚወሰደው ፕሪንተር ማስሞክር፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውስድ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፤ ቫትን ያላካተተ ዋጋ ቫት እንደተጨመረ ተደርጐ ስለሚወሰድ፤ አልጨመርኩም ወይም ይጨመረበት የሚል ተጫራች ቢኖር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናል በማድረግ በየሎቱ በፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመቤታችን የግ/ፋ/ን/አ ቡድን በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከህዳር 7/2019 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ16/03/2019 ዓ.ም 11፡30 ታሽጎ በ17/03/2019 ከጠዋቱ በ3፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው ተከፍቶ በግዥ መመሪያው ቁጥር 144/2018 መሰረት ተገዥ የመሆን ወይም የመቀበል ግዴታ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለክላስተር ማእከሉ ማሳወቅ አለባቸው፡
  12.  በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ማድረግ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  13. ተጫራቾች በሎት ምድብ 1-2 ያሉትን እቃዎች ለእያንዳንዳቸው የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 3000 (ሶስት ሽህ ብር) ብቻ ከሎት ምድብ 3 የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 10000 (አስር ሽህ ብር)ብቻ ከሎት ምድብ 4-5 ያሉትን እቃዎች ለእያንዳንዳቸው የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 1000 (አንድ ሽህ ብር) ብቻ ሎት ምድብ 6 የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 5000 (አምስት ሽህ ብር) ብቻ በሎት ምድብ 7 በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ በሁኔታ ላይ የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋስትና በማስያዝ ኦርጅናሉን በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ክፍያ ቢጠይቁ መ/ቤቱ አያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዲያስረከቡ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል።
  15. በተጨማሪም በጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ እቃው በገበያ ላይ የለም የሚል ምክንያት ተቀባይነት የለውም፡፡
  16. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል በህግም ያስጠይቃል፡፡
  17.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 431 51 15 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወልዲያ ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ካላስተር ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-11-25
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid opening: 2026-11-26 09:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Woldia Cluster Occupational Competency Assessment and Certification Center
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:30:15.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders