Stationery

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግጨ 02/2019


የአብክመ ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ አላቂና ቋሚ ዕቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ማሟላት ያለባቸው፡-

1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ11 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት 11ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች

  • ለሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ብር 10,000፣
  • ለሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች ብር 50,000፣
  • ለሎት 3. የቢሮና የቤት ዕቃዎች ብር 100፣
  • ለሎት 4.1 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 250,000፣
  • ለሎት 4.2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ዝርዝር መግለጫ የሌላቸው) ብር 3,500፣
  • ለሎት 5. የተሸከርካሪ ማስዋቢያ ብር 12,500፣
  • ለሎት 6. የደንብ ልብስ ብር 2,900፣
  • ለሎት 7. ጫማ (የደንብ ልብስ) ብር 2,700፣
  • ለሎት 8. የብስክሌት ጎማ ብር 800፣
  • ለሎት 9. የተሸከርካሪ ጎማ ብር 44,600፣
  • ለሎት 10. የህትመት ስራ ብር 9,400፣
  • ለሎት 11. የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ብር 2,600፣
  • ለሎት 12. የተለያዩ የደንብ ልብሶች ብር 380፣
  • ለሎት 13. የውሃ ዕቃ ብር 3,000፣
  • ለሎት 14. ቦርሳ ብር 3,500፣
  • ለሎት 15. የኤሌክትሪክ ዕቃ ብር 30,000 እና
  • ለሎት 16. የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ብር 6,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ/አገልግሎት አይነት ቢሮው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡

7. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

9. ለበለጠ መረጃ፡- አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 /058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Finance and Economic Cooperation Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:22:56.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders