Textile, Garments and Uniforms

በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጃናሞራ ወረዳ ፍ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጃናሞራ ወረዳ ፍ/ቤት

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ የተዘጋጁ አልባሳት ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ፣
  • ሎት 3 ህትመት፣
  • ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እና
  • ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. በእያንዳንዱ ሎት እቃዎችና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ከግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/ቡደን መሪ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት ገዝተው መወስድ ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ በየአንዳንዱ ሎት የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) (ቢድ ቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ጨረታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከህዳር 7/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም የሚቆይ መሆኑ ታውቆ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት መጥተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን/መሪ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ህዳር 17/2019 ዓ/ም በእለቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጎ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 8 ጃናሞራ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ//መሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ህዳር 7/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 16/2019 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ጨረታው የሚከፍትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ውድቅ ይሆናል፡፡

13. ተጫራቾች ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድና ፖስታ ላይ የድረጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ፣ ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡

16. ተጫራቾች የእቃ ርክክቡ ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በማምጣት የሚያስረክቡ ሲሆን የትራንስፖርቱ ወጭ እንዲሁም ማስጫኛና ማውረጃ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡

17. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ/ፍ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 294 02 26 /09 18 22 64 89 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-11-26 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Janamora Woreda Court
  • Bid bond: 1% በእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:24:18.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders