Stationery

የሊበን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አላቂ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


ሰሜን ጎጃም ዞን የሰ//አቸ/ወረዳ የሊበን መጀመሪያ ደረጃ በሆስፒታል አገልግሎት የሚዉሉ

  • ሎት1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት2. የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት3. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት4. ህትመት
  • ሎት5. የመጸዳጃ ቤት ማስመጠጥ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፤

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር በፖስታ አሽገዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ21 የስራ ቀናት ድረስ ተሸጦ በ22ኛዉ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ በዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን በሊበን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ወይም የዋጋ መሙያ ቅፅ ከሊበን የመ/ደ/ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 አንድ መቶ ብር እየከፈሉ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9.  የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነብብ መሆን የለበትም፡፡ ሆኖም ግን ስረዝ ካለዉ ፊትለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ዉጭ ይደረጋሉ፡፡
  10. በጨረታዉ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ በሊበን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስተዳደር ግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 09 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11.  አሸናፊው የሚለየዉ በተሞላው ጠቅላላ ዋጋ ነዉ፡፡
  12. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃጸም በመመሪያዉ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝና ኦርጅናል ማስረጃ በማስገባት ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር በፖስታ አሽገዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-09 27 82 94 29፣09 18 18 63 75 ወይም 09 25 33 27 91 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሊበን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-12-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ21 የስራ ቀናት ድረስ ተሸጦ በ22ኛዉ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-10 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ21 የስራ ቀናት ድረስ ተሸጦ በ22ኛዉ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Liben Primary Hospital
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:28:14.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders