Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች የ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአቅርቦት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች የ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የአቅርቦት ግዥዎች ማለትም፡-

  • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 4. የውጭ ፈርኒቸር አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 5. የመኪና ጎማ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 6. የውሀ ተቋማት ግንባታ ቁሳቁስ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 7. የተዘጋጁ ጫማዎች አቅርቦት ግዥ፣
  •  ሎት 8. የተዘጋጁ ልብሶች አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 9. ብትን ጨርቅ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 10. የስፖርት ቁሳቁስ አቅርቦት ግዥ፣
  • ሎት 11. የስፖርት አልባሳትና ጫማ አቅርቦት ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ጨረታው ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ ለመሆኑ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚገዛው እቃ መጠን፣ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ሎት 1. ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሽህ ብር)፣| ሎት 2 ብር 6,000 (ስድስት ሽህ ብር)፣ ሎት 3. ብር 30,000(ሰላሳ ሽህ ብር)፣ ሎት4. ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር)፣ ሎት 5. ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር)፣ ሎት 6. ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሽህ ብር)፣ ሎት 7. ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር)፣ ሎት 8. ብር 25,000 (ሀያ አምስት ሽህ ብር) ሎት 9. ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) ሎት 10. ብር 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር)፣ ሎት 11. ብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት (lettir of credit) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሚያሥይዙ ከሆነ ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ ስምና አድራሻ በማስቀመጥ ደም/ዙ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ የጨረታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 07/2019 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. በተራ ቁጥር 11 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 773 02 74 /058 773 00 36 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 07/2019 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 07/2019 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dembecha Localities Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T14:17:06.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders