Equipment and Accessories

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ዕቃዎች የሚገዛላቸው የትምህርት ክፍሎት

  1. ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጅ ዲ/ት
  2. ኤሌከትርካል ኤሌክትሮንግስ ዲ/ት
  3. አኒማል ፕሮዳከሽን ዕቃዎች
  4. ሆቴል ዲቤት ዕቃዎች
  5. ጋርመንት ዲት ዕቃዎች
  6. የጸጉር ሥራ ዲፓርትመንት ዕቃዎች
  7. የህጻናት ማቆያ ዕቃዎች
  8. ለጋራ አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብሶች
  9. የመኪና መለዋወጫዎች እና ጎማዎች
  10.  የጽዳት ዕቃዎች እና መጋረጃዎች

በመሆኑም ከላይ ለተዘረዘሩ የሥልጠና ዘርፎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ለመወዳደር የምትፈልጉተወዳዳሪዎች አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ጨረታውን ተወዳደሪ/ አቅራቢ ድርጅት የ2019 ዓም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል ።
  2. የገንዘብና ኢኮ/ል/ሚኒስተር ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እስት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው
  4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎችን ገዥው መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው
  5. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ዋጋው ከቫት ውጭና ከነቫቱ በፊት ተብሎ በጥራት መሞላት ይኖርበታል። እንዲሁም ቫት ከተካተተበት ተካቶበታል ተብሎ እንዲሁም ያልተካተተ ከሆነ አልተካተተም ተብሎ ሊጻፍ ይገባዋል ይህ ሳይሆን ቢቀር ቫት እንደተካተተ አድርጎ መ/ቤቱ የሚወስድ መሆኑንእናሳውቃለን ።
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 2 % ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት::
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከፖሊ ኮሌጁ ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበርያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል። በተጨማሪ ያሽነፈበትን ዕቃ በ5 ቀናት ውስጥ ለኮሌጁ የማቅረብ ግዴታ አለበት።ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት 10 % ገንዘብ በቀጥታ ለፖሊ ኮሌጁ ገቢ ሆኖከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
  9. የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ከኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር ብሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር በኮሌጁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኣካውንት ቁጥር GOV 100001929478 በማስገባትና አድቫይስ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛትይጠበቅበታል ::
  10. ተጫራቾች የሚቀርቡትን የመወዲደርያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ማህተም አሳርፎበት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  11. ጨረታው በ16 ቀን ከጠዋቱ 3.30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። በተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመግኘታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463312719 ወይም 0463313848 ይደውሉ::

የዲላ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-12-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16 ቀን ከጠዋቱ 3.30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-02 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ16 ቀን ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Dilla Poly Technic College
  • Bid bond: የጠቅላላ ዋጋ 2% ብር 10,000.00
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T10:46:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders