Water Well Drilling
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ ኢንስታሌሽን በጅዳ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የተጫራቾች መመሪያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ ኢንስታሌሽን በጅዳ ወረዳ ቀበሌዎች ውስጥ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
በዚሁ መሰረት ፤- የጅዳ ወረዳ ውሃ እና እነርጂ ጽ/ቤት ሻሎዌል (Shallow well) ቁፋሮ እና ሙሉ እንስታሌሽን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስቆፈር እና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን የሰው ሀይል እና ማቴሪያል አሟልቶ ለማሰራት ፍቃደኛ የሆኑትን የሥራ ተቋሯጮችን ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት የጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ መወዳደር እንዲችሉ ፤-
1. ድርጅቱ ለ2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፡የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤የግብር ክሊራንስ (tax clearance) እና (Tin number) ቲን እና (Drilling license) እና በስራ ዘርፍ (Drilling well) 5 ደረጃ እና ከዚያ በላይ ያለው መሆን አለበት እንዲሁም ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በውሃ ጉድጓድ (water well) ዘርፍ ያለው መሆን አለበት።
2, ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ (ማለትም ከ2014-2018 ዓ.ም ድረስ)የሚያሳይ የስራ ልምድ (water well Drilling license) ከሚመለከተው አካል ላይ ማቅረብ አለበት እንዲሁም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. ማንኛውም ተጫራች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው 5 እና ከዛ በላይ (1-5)የሚያሳይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ በውሃ ጉድጓድ ዘርፍ (water well Drilling license) ማቅረብ አለበት።
4. ማንኛውም ተጫራች ለውሃ ጉድጓድ water well ቁፋሮ የሚያገለግል ማሽን ያለው መሆኑን የሚያሳይ ሊብሬ(libre) ያለው ወይም ውክልና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት
5. ተጫራቹ ለውሃ water well 60 ሜትር ወደ ታች መቆፈር ያለበት ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ 10 ሜትር ጥልቀቱን መጨመር ወይም መቀነስ (60+-10) ይችላል።
6. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ የሚያገለግል ሁሉንም የማሽን አይነት ያለውና የድርጅቱን የሰው ሀይል እና የስራ ድርሻውን የሚገልፅ ፐሮፋይል ማቅረብ የሚችል።
7. ተጫራቹ ለውሃ water well ቁፋሮ apron (well head) የሚያገለግሉ ሁሉንም ዕቃዎችን እና ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለራሱ ማቅረብ አለበት።
8. ተጫራቾች የአጅ ዋጋ እና የእቃ ዋጋ (material cost and labour cost) አንድ ላይ መሙላት አለባቸው።
9. ተጫራቹ Well completion report and water test quality report ) ማቅረብ አለበት።
10, ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር )ብቻ በካሽ፤በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ለጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት በማለት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
11. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በሰም ለየብቻ በማሸግ እና CPO ለብቻ በማሸግ እነዚህን 3 ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ (mother envelope) በሠም : በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡በተጨማሪ እያንዳንዳቸው ዶክመንት ላይ ኦርጂናል እና ኮፒ፤የድርጅቱ ማህተም ማድረግ እንዲሁም CPO በማለት በፖስታው ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
12. አሸናፊው ድርጅት ለስራ ማስጀመሪያ ቅድመ ክፍያ (Advance payment) ለመውሰድ ከማንኛውም ባንክ (unconditional bank guaranty) ማቅረብ አለበት።
13. አሸናፊው ድርጅት ለስራው ክፍያ ሰነድ (payment certificate) በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ አለበት።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ተጫራቾች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረደ ገንዘብ ጽ/ቤት በማቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 07/04/2019 ዓ.ም. ድረስ በጅዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
16. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ እስከ 08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
17, ጨረታው በዚሁ እለት ማለትም በ08/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻተው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
18. ተጫራቾች የተሟላ ሰነድ መግዛታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
19. ከጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
20. ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተራጋገጠ ሲፒኦ CPO/ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
ስ.ቁ 0116 736 328
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ውሃ እና ኢነርጂ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-12-17 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Jida Woreda Water & Energy Resource Development Office
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 18, 2026)
- Posted at: 2026-11-18T08:18:59.000Z
- Source: Qelal Tenders