Textile, Garments and Uniforms

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ላሉ ተቋማቶች አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ እና ጫማዎች እንዲሁም የስራ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨ /መ/ቁ ግዥ / ን/ማ 512/የመ/ግ/ጨ/003/19

በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ላሉ ተቋማቶች አገልግሎት የሚውል

  • ሎት-1 የጤና ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፤
  • ሎት 2 ለስራ አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ እና
  • ሎት-3 ለጤና ባለሙያዎች እና ለድጋፍ ሰጪዎች የሚውል የደንብ ጫማዎች እና የስራ መሳሪያዎች ግዢ በማእቀፍ ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያውን አውጥቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

1/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3/ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

4/ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሠነዱን በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቁጥር 109 ቀርበው ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500.00 (አምስት መቶ) መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጨረታ መክፈቻው እለት የጨረታ ሠነዱን በትክክል ሞልተው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዋናውንና ኮፒውን በአግባቡ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

5/ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዛው ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 215 በግልጽ ሲከፈት፤ ቀኑ በዓል ወይም የዕረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

6/ ተጫራቾች ለሎት-1 ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ፤ለሎት-2 ብር100.000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ለሎት-3 ብር50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8/ ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ቢያስፈልግ በሚመለከተው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግለሎት ጽ/ቤት ቢሮቁጥር 215

የስልክ ቁጥር:- 09 15 76 19 64 / 09 23 32 32 42
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-12-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 18, 2026)
  • Posted at: 2026-11-18T11:18:42.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders