Machinery and Equipment
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የብሄራዊ የአቮካዶ ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል የአቮካዶ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲከ ባለ 20፣ መጋዝ መክተቢያ ሰንጢ እና መገረዣያ መቀስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የብሄራዊ የአቮካዶ ፕሮግራም አገልግሎት የሚውል
- ሎት 01 የአቮካዶ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲከ ባለ 20፣
- ኦት 02 የእርሻ መሳሪያ ጋሪ መግረዣ መጋዝ መክተቢያ ሰንጢ እና መገረዣያ መቀስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ መታደሱን የሚገልፅ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (ፐIN) ያላቸሁ: እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ወይም በኢጂፒ የተመዘገበ፣
3. የግዥው መጠን ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5 የሚገዙ የአቮካዶ ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ ብር በቁርጥ ሎች 01 የአቮካዶ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 20 ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺ ብር/ ሎት 02 ለአርሻ መሳሪያ ጋሪ መገረዣ መጋዝ እና መከተቢያ ሰንጢ እና መገረዣ መቀስ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የመወዳዳሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነዱን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 027 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 11ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 27 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 5849/ 058 320 8095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ኣይኖረውም።
12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-11-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-30 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Amhara National Regional State Agricultural Bureau
- Bid bond: 500,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 19, 2026)
- Posted at: 2026-11-19T08:50:21.000Z
- Source: Qelal Tenders