Other Sales

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 07/2019

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣ አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች እና ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ በሐራጅ ጨረታው መክፈቻ ቀን ይዘዉ መቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ አየር ላይ ከዋለበት ከ10/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት የጉምሩክ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

2. ተጫራቾች በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 01 ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ምድብ 03 ልዩ ልዩ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር)፣ ለምድብ 4 ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)፣ ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000(ሃምሳ ሽ ብር)፣ ለምድብ 6 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሽ ብር)፣ ምድብ 07 ንፅህና መጠበቂያ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ) ፣ ምድብ 08 ስፔርፓርት ዘርፍ ዕቃዎች ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ብር)፣ ምድብ 09 አልባሳት ዘርፍ ዕቃዎች ብር 30,000፣ ምድብ 10 ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 70,000 (ሰባ ሺ ብር) (ሰላሳ ሺ) እና ለምድብ 11 ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ C.P.O በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 15/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መገኘት አለባቸው።

3. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው ዓይነት

የጨረታ የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

ሀራጅ ጨረታ

እስከ 15/03/2019 ዓ.ም

15/03/3019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል።

4. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3(ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6. አሽናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ፡- 033 559 0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-24 10:00
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 19, 2026)
  • Posted at: 2026-11-19T10:09:27.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders